የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ብይን አዛወረ | ከይር ታይምስ
አምዶች
የቅርብ ዜና
ደቡብ ሱዳን ከዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ ምርጫ ልታካሂድ ቀጠሮ ቆረጠች ግዙፉ የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂ ከ75 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከኢትዮጵያ ሊወጣ ነው ባይናንስ በኢትዮጵያ ውስጥ አቋርጦት የነበረውን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት አገልግሎት በድጋሚ ጀመረ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ብይን አዛወረ በኬንያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የወሮበላነት ፖለቲካ (Goonism) በመባል የሚታወቀው ተግባር፣ በተደራጀ መልክ ተዋቅሮ ዳግም ማንሰራራቱ ተገለጠ። የመካከለኛው ምስራቅ ባሩድ ተቀሰቀሰ፡ ኢራን መርከቦች ወደ ሆርሙዝ እንዳይጠጉ አስጠነቀቀች ህወሃት በአሜሪካ የቪዛ ገደብ ላይ ያለውን ቅሬታ ገለጸ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርም ጠየቀ በትምህርት ላይ ያረበበው የጦርነት ጥላ፡ በኢትዮጵያ የነገይቱ ተስፋዎች መፃኢ ዕድል ሲፈተን የመንግስት ካዝና እስከመቼ ይዘረከረካል? 15 ቢሊዮን ብር ያላግባብ የያዙት ተቋማት በሕግ ፊት ይቁሙ! አዲሱ የሕወሓት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግጭት 600 ሺህ ሰዎችን የበላውን ጦርነት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ስጋት ፈጠረ ደቡብ ሱዳን ከዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ ምርጫ ልታካሂድ ቀጠሮ ቆረጠች ግዙፉ የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂ ከ75 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከኢትዮጵያ ሊወጣ ነው ባይናንስ በኢትዮጵያ ውስጥ አቋርጦት የነበረውን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት አገልግሎት በድጋሚ ጀመረ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ብይን አዛወረ በኬንያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የወሮበላነት ፖለቲካ (Goonism) በመባል የሚታወቀው ተግባር፣ በተደራጀ መልክ ተዋቅሮ ዳግም ማንሰራራቱ ተገለጠ። የመካከለኛው ምስራቅ ባሩድ ተቀሰቀሰ፡ ኢራን መርከቦች ወደ ሆርሙዝ እንዳይጠጉ አስጠነቀቀች ህወሃት በአሜሪካ የቪዛ ገደብ ላይ ያለውን ቅሬታ ገለጸ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርም ጠየቀ በትምህርት ላይ ያረበበው የጦርነት ጥላ፡ በኢትዮጵያ የነገይቱ ተስፋዎች መፃኢ ዕድል ሲፈተን የመንግስት ካዝና እስከመቼ ይዘረከረካል? 15 ቢሊዮን ብር ያላግባብ የያዙት ተቋማት በሕግ ፊት ይቁሙ! አዲሱ የሕወሓት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግጭት 600 ሺህ ሰዎችን የበላውን ጦርነት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ስጋት ፈጠረ
ዜና / የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ብይን አዛወረ

በያፌት ግርማ | June 23, 2026

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና በአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለው ላይ ዛሬ ሊሰጥ የነበረውን ብይን ለሌላ ጊዜ ማዛወሩ ተገለጠ። ፍርድ ቤቱ ብይኑን ለመስጠት ለሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ሸገር ዘግቧል።

​ተከሳሾቹ ቀደም ሲል በማረሚያ ቤት ውስጥ የሕክምና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዳልተከበረ፣ እንዲሁም በቤተሰብ የመጎብኘት ሰብአዊ መብታቸው መጣሱን በመጥቀስ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ይህንን ተከትሎ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ዛሬ ለችሎቱ ምላሽ መስጠታቸውን የደረሰን ዘገባ ያመላክታል።

​የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች በሰጡት ምላሽ፣ ተከሳሾቹ ያቀረቧቸውንና ያጋጠሟቸውን ችግሮች በሙሉ መፍታታቸውን ለችሎቱ በማስረዳት ክርክር አቅርበዋል። ሆኖም ግን ተከሳሾቹ በበኩላቸው የተጠቀሱት ችግሮች አሁንም ድረስ እንዳልተፈቱና መብቶቻቸው እየተጣሱ መሆኑን ለችሎቱ በድጋሚ ተናግረዋል።

​ችሎቱ በጉዳዩ ላይ ተከሳሾቹ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ከማረሚያ ቤቱ አቅም በላይ እንዳልሆኑ በመግለጽ፣ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች የቀሩትን ችግሮች በአስቸኳይ እና በቅንነት እንዲፈቱ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙን የደረሰን ዘገባ ያረጋግጣል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ