ባይናንስ በኢትዮጵያ ውስጥ አቋርጦት የነበረውን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት አገልግሎት በድጋሚ ጀመረ | ከይር ታይምስ
አምዶች
የቅርብ ዜና
ደቡብ ሱዳን ከዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ ምርጫ ልታካሂድ ቀጠሮ ቆረጠች ግዙፉ የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂ ከ75 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከኢትዮጵያ ሊወጣ ነው ባይናንስ በኢትዮጵያ ውስጥ አቋርጦት የነበረውን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት አገልግሎት በድጋሚ ጀመረ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ብይን አዛወረ በኬንያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የወሮበላነት ፖለቲካ (Goonism) በመባል የሚታወቀው ተግባር፣ በተደራጀ መልክ ተዋቅሮ ዳግም ማንሰራራቱ ተገለጠ። የመካከለኛው ምስራቅ ባሩድ ተቀሰቀሰ፡ ኢራን መርከቦች ወደ ሆርሙዝ እንዳይጠጉ አስጠነቀቀች ህወሃት በአሜሪካ የቪዛ ገደብ ላይ ያለውን ቅሬታ ገለጸ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርም ጠየቀ በትምህርት ላይ ያረበበው የጦርነት ጥላ፡ በኢትዮጵያ የነገይቱ ተስፋዎች መፃኢ ዕድል ሲፈተን የመንግስት ካዝና እስከመቼ ይዘረከረካል? 15 ቢሊዮን ብር ያላግባብ የያዙት ተቋማት በሕግ ፊት ይቁሙ! አዲሱ የሕወሓት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግጭት 600 ሺህ ሰዎችን የበላውን ጦርነት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ስጋት ፈጠረ ደቡብ ሱዳን ከዓለም አቀፍ ግፊት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ ምርጫ ልታካሂድ ቀጠሮ ቆረጠች ግዙፉ የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ቶታል ኢነርጂ ከ75 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከኢትዮጵያ ሊወጣ ነው ባይናንስ በኢትዮጵያ ውስጥ አቋርጦት የነበረውን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት አገልግሎት በድጋሚ ጀመረ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ሊሰጥ የነበረውን ብይን አዛወረ በኬንያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የወሮበላነት ፖለቲካ (Goonism) በመባል የሚታወቀው ተግባር፣ በተደራጀ መልክ ተዋቅሮ ዳግም ማንሰራራቱ ተገለጠ። የመካከለኛው ምስራቅ ባሩድ ተቀሰቀሰ፡ ኢራን መርከቦች ወደ ሆርሙዝ እንዳይጠጉ አስጠነቀቀች ህወሃት በአሜሪካ የቪዛ ገደብ ላይ ያለውን ቅሬታ ገለጸ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርም ጠየቀ በትምህርት ላይ ያረበበው የጦርነት ጥላ፡ በኢትዮጵያ የነገይቱ ተስፋዎች መፃኢ ዕድል ሲፈተን የመንግስት ካዝና እስከመቼ ይዘረከረካል? 15 ቢሊዮን ብር ያላግባብ የያዙት ተቋማት በሕግ ፊት ይቁሙ! አዲሱ የሕወሓት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግጭት 600 ሺህ ሰዎችን የበላውን ጦርነት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ስጋት ፈጠረ
ቢዝነስ / ባንክ እና ፋይናንስ

ባይናንስ በኢትዮጵያ ውስጥ አቋርጦት የነበረውን የክሪፕቶ ከረንሲ ግብይት አገልግሎት በድጋሚ ጀመረ

በሮቤል ሙላቱ | June 23, 2026

በኢትዮጵያ ውስጥ አገልግሎቱን አቋርጦ የነበረው ዓለም አቀፉ የክሪፕቶ ከረንሲ መገበያያ መድረክ ባይናንስ (Binance)፣ አቋርጦት የነበረውን አገልግሎት በአገሪቱ ውስጥ በድጋሚ መጀመሩን ይፋ አደረገ። ኩባንያው ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በመስራት አገልግሎቱን በድጋሚ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

​ባይናንስ አገልግሎቱን በድጋሚ ለመጀመር የቻለው፣ ከአገሪቱ የክሪፕቶ ከረንሲ ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ በደረሰበት ስምምነትና መግባባት መሰረት መሆኑን በገለጻው ላይ ጠቅሷል። ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ዲጂታል የገንዘብ ግብይትን ለሚጠቀሙ ዜጎች አዲስ በር የሚከፍት ሆኗል።

​ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ገንዘብ (ብር) ከክሪፕቶ ከረንሲ ያልተማከለ ግብይት ለመለየትና ለመጠበቅ የሚያስችሉ ጠንካራ የሕግና የቁጥጥር እርምጃዎችን መውሰድ መጀመሩ ይታወሳል።

ይህንን የመንግስትን አቋምና እርምጃ ተከትሎ፣ ባይናንስ እና የቴሌግራም ዋሌትን (Telegram Wallet) የመሰሉ ዓለም አቀፍ የክሪፕቶ መገበያያ መድረኮች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰጡትን ስራ ማቋረጣቸውን ዋዜማ ቀደም ሲል መዘገቧ ይታወሳል። አሁን ግን አዳዲስ መመሪያዎችን በማክበር ስራው በይፋ ተጀምሯል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ