አምዶች

Logo ከይር ታይምስ

የዲጂታል ዜና እምብርት

የቅርብ ዜና
ህወሓትን ከሥልጣን ለማስወገድ ያለመው አዲሱ ምክር ቤት እና የጀነራሎቹ ወታደራዊ ስልት የሕዝብ እንደራሴዎች ወይስ የፖለቲካ ምስጢረኞች? ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የዕዳ መልሶ ማዋቀሪያ ሥርዓት በአስቸኳይ እንዲሻሻል ጠየቀች መንግስት ከሕዝብ እይታ የሸሸገውን የፋይናንስ ምንጭ በግልጽ ለሕዝብ ይፋ ሊያደርግ ይገባል FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS የማክሮን የአፍሪካ ጉዞ እና የኃያልነት ስጋት ቻይና ከአሜሪካ ነዳጅ ለመግዛት ተስማማች፤ ትራምፕ የቤጂንግ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ የሥልጣን ገደብ ሕጋዊ ማዕቀፍ፦ የእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማሻሻያ ወይስ የተሰላ የፖለቲካ ስትራቴጂ? የትግራይ ፕሬዝዳንት በሳውዲ አረቢያ ለሞት የተፈረደባቸው ዜጎች ምህረት እንዲደረግላቸው ተማጸኑ የቀይ ኩሬው ምስጢር እና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ህወሓትን ከሥልጣን ለማስወገድ ያለመው አዲሱ ምክር ቤት እና የጀነራሎቹ ወታደራዊ ስልት የሕዝብ እንደራሴዎች ወይስ የፖለቲካ ምስጢረኞች? ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የዕዳ መልሶ ማዋቀሪያ ሥርዓት በአስቸኳይ እንዲሻሻል ጠየቀች መንግስት ከሕዝብ እይታ የሸሸገውን የፋይናንስ ምንጭ በግልጽ ለሕዝብ ይፋ ሊያደርግ ይገባል FIFTY MAJOR POLITICAL THINKERS የማክሮን የአፍሪካ ጉዞ እና የኃያልነት ስጋት ቻይና ከአሜሪካ ነዳጅ ለመግዛት ተስማማች፤ ትራምፕ የቤጂንግ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ የሥልጣን ገደብ ሕጋዊ ማዕቀፍ፦ የእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማሻሻያ ወይስ የተሰላ የፖለቲካ ስትራቴጂ? የትግራይ ፕሬዝዳንት በሳውዲ አረቢያ ለሞት የተፈረደባቸው ዜጎች ምህረት እንዲደረግላቸው ተማጸኑ የቀይ ኩሬው ምስጢር እና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ
ነፃ ሃሳብ / አስተያየት

የሕዝብ እንደራሴዎች ወይስ የፖለቲካ ምስጢረኞች?

ያፌት ግርማ | May 18, 2026

የፓርላማው የሚዲያ ከልከላ እና የዲሞክራሲው መጋረጃ መቀደድ

በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ፓርላማ የሕዝብ ድምፅ የሚሰማበት፣ የመንግሥት አሠራር የሚገመገምበትና ግልጽነት የሚነግሥበት የመጨረሻው የሕዝብ አምባ ነው። ነገር ግን በኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው አካሄድ ከዚህ በተቃራኒው የቆመ ሆኗል። 

ምክር ቤቱ መደበኛና የቋሚ ኮሚቴ ስብሰባዎቹን ለግል መገናኛ ብዙሃን ዝግ በማድረግ፣ የሕዝብን መረጃ የማግኘት መብት በይፋ እየገደበ ይገኛል።

የሕግ የበላይነትን እናስከብራለን የሚሉ አካላት ራሳቸው የደነገጉትን ሕግ ጥሰው፣ ጋዜጠኞችን ከበር ሲያባርሩ ማየት አገሪቱ ወደ የትኛው የፖለቲካ አቅጣጫ እየተጓዘች እንደሆነ ማሳያ ነው።

በኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 58 (5) እና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው፤ የምክር ቤቱ ስብሰባዎች በሙሉ በግልጽ መካሄድ አለባቸው። 

ስብሰባን ዝግ ማድረግ የሚቻለው በሕግ አስፈጻሚው ወይም በአባላት ተጠይቆ፣ ከግማሽ በላይ በሆነ የምክር ቤቱ አባላት ድምፅ ሲደገፍ ብቻ ነው።

አሁን ግን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም። ፓርላማው ለምን የግል ሚዲያዎችን እንደከለከለ በይፋ የሰጠው ማብራሪያም ሆነ ያስተላለፈው የውሳኔ ድምፅ የለም። ይህ የሚያሳየው ተቋሙ በሕግና አሠራር ሳይሆን፣ በጥቂት ግለሰቦች ፍላጎትና “ትእዛዝ” እየተመራ መሆኑን ነው።

አንዱን የመንግሥት ልሳን ፈቅዶ፣ የግል ሚዲያዎችን መከልከል ደግሞ አድሏዊነት ብቻ ሳይሆን፣ ነፃ ጋዜጠኝነትን የመቅበር ፍላጎት ነው።

ለመሆኑ በፓርላማው በር ላይ መጋረጃ እንዲጣል የተፈለገው ምን ምስጢር ስላለ ነው? ዝግ በተደረጉት ስብሰባዎች ውስጥ የተገመገሙት የገንዘብ፣ የጤና፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴሮች እንዲሁም የልማት ባንክ የዘጠኝ ወር ሪፖርቶች ናቸው። እነዚህ ተቋማት የሕዝብን ገንዘብና ጥቅም የሚያስተዳድሩ እንደመሆናቸው፣ አፈጻጸማቸው ለሕዝብ ግልጽ ሊሆን ይገባ ነበር።

ከዚህ የከፋው ተቃርኖ ግን “የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ” በዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲወያይበት፣ ውይይቱ ለግል መገናኛ ብዙሃን ዝግ መደረጉ ነው። መረጃን ስለመፍቀድ የሚመክር አዋጅ፣ መረጃን በመከልከል ሲጀመር ማየት እጅግ አስቂኝ እና አሳዛኝ ክስተት ነው።

ይህ አካሄድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህሩ አብዲሳ ዘርዓይ (ዶ/ር) ለሸገር ራዲዮ እንደገለፁት፦ “እኔ ከመረጥኳቸው ውጪ እዚያ አካባቢ ዞር አትሉም" ማለት የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት የሚሸረሽር ድርጊት ነው ብለዋል።

በዚህ መሀል እንደ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ያሉ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አጋዥ ተቋማት ያሳዩት ዳተኝነት ሌላው የሚዲያውን ክንፍ የሰበረ ክስተት ነው።

ሸገር እንደዘገበው የእንባ ጠባቂ ተቋም “በደብዳቤ የደረሰኝ ቅሬታ የለም፣ ስለዚህ አልተከታተልኩም” ማለቱ የቢሮክራሲ ሰበብ እንጂ የኃላፊነት ስሜት አይደለም።

ኢሰመኮም በተመሳሳይ “ክትትል አላደረግኩም፣ አስተያየት አልሰጥም” በሚል እጁን አጣጥፎ መቀመጡን ሸገር ራዲዮ ነገሮናል። አገር አቀፍ የሚዲያ ከልከላ እየተካሄደ፣ ጋዜጠኞች ከፓርላማ በር ላይ እየተባረሩ፣ ተቋማቱ “ማስረጃ በደብዳቤ አልመጣልኝም” በሚል ሰበብ ዝምታን መምረጣቸው፣ የቁጥጥር ሥርዓቱ ምን ያህል እንደደነዘዘ ያሳያል።

በአጠቃላይ የዜጎች መብት አደጋ ላይ ነው። የመገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታምራት ኃይሉ እንዳሉት፤ መረጃ የማግኘት መብት ለጋዜጠኞች ብቻ ሳይሆን “ለሁሉም ዜጎች” የተፈቀደ ሰብዓዊ መብት ነው። ሚዲያዎችን መከልከል ማለት ሕዝቡ የላካቸው እንደራሴዎች ምን እየሠሩለት እንደሆነ እንዳያውቅ ዓይኑን ማወር ማለት ነው።

መንግሥት በሕግ የደነገገውን የመረጃ ነፃነት የማክበር ግዴታ አለበት። ፓርላማው የሕዝብ ተወካዮች መሰብሰቢያ መሆኑ ቀርቶ በጥቂት ባለሥልጣናት ፈቃድ ብቻ የሚንቀሳቀስ “የምስጢር ቤት” ከሆነ፣ የዲሞክራሲ ሥርዓቱ መሞቱን አውጆ መጋረጃውን ሙሉ በሙሉ መዝጋት ይሻላል። ካልሆነ ግን፣ ይህ ሕገ-ወጥ እገዳ በአስቸኳይ አንስቶ፣ የፓርላማው በር ለነፃ ጋዜጠኞች ክፍት ሊሆን ይገባል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ