አምዶች

Logo ከይር ታይምስ

የዲጂታል ዜና እምብርት

የቅርብ ዜና
ምርጫ ቦርድ የዕጩ ይስሃቅ ወልዳይን ራስን ከምርጫ የማግለል ውሳኔ ውድቅ አደረገ “የኮከቡ ሰው” የተሰኘው አዲስ ተውኔት ነገ በዓለም ሲኒማ ለተመልካች ሊቀርብ ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆኑ እስራቶችና የመብት ጥሰቶች አሁንም አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ ገለጸ ፌደራል ፖሊስ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠየቀ የለንደን ሰማይ በደስታ ቀልቷል፡ የአርሰናል የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቅ ያበቃበት ያ ታሪካዊ ምሽት “የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል”፤ መምህር ታዬ ቦጋለ የፖሊሲ ነፃነት ሚስጥር፤ ኢትዮጵያ ቁልፍ መረጃዎቿን በራሷ እጅ ማድረጓ ምን ትርጉም አለው? 'ምንም የሚተርፍ ነገር አይኖርም’ የትራምፕ ለኢራን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ህወሓትን ከሥልጣን ለማስወገድ ያለመው አዲሱ ምክር ቤት እና የጀነራሎቹ ወታደራዊ ስልት ምርጫ ቦርድ የዕጩ ይስሃቅ ወልዳይን ራስን ከምርጫ የማግለል ውሳኔ ውድቅ አደረገ “የኮከቡ ሰው” የተሰኘው አዲስ ተውኔት ነገ በዓለም ሲኒማ ለተመልካች ሊቀርብ ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆኑ እስራቶችና የመብት ጥሰቶች አሁንም አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ ገለጸ ፌደራል ፖሊስ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠየቀ የለንደን ሰማይ በደስታ ቀልቷል፡ የአርሰናል የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቅ ያበቃበት ያ ታሪካዊ ምሽት “የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል”፤ መምህር ታዬ ቦጋለ የፖሊሲ ነፃነት ሚስጥር፤ ኢትዮጵያ ቁልፍ መረጃዎቿን በራሷ እጅ ማድረጓ ምን ትርጉም አለው? 'ምንም የሚተርፍ ነገር አይኖርም’ የትራምፕ ለኢራን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ህወሓትን ከሥልጣን ለማስወገድ ያለመው አዲሱ ምክር ቤት እና የጀነራሎቹ ወታደራዊ ስልት
ዜና / የሀገር ውስጥ ዜና

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ

ማስረሻ ቢተዉ | May 20, 2026

የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ ዓለም አቀፍ አጋሮችና የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት የነዳጅና ማዳበሪያ መግዣ እንዲሁም ለአነስተኛ አርሶ አደሮች መደጎሚያ የሚሆን አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

ሚኒስትሩ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት ትናንት በለንደን በተካሄደው የግሎባል ፓርትነርሺፕ ኮንፈረንስ (Global Partnership Conference) ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር መሆኑን በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

​ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈጠረው የማዳበሪያ አቅርቦት ማሽቆልቆል እና የምርት ወጪዎች መጨመር ታዳጊ አገራትን ክፉኛ እየጎዳ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ተግዳሮት በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ላይ የሚከተሉትን ከፍተኛ ስጋቶች እንደሚደቅን አስገንዝበዋል፦

​የምርታማነት መቀነስ፦ የማዳበሪያ አቅርቦት መስተጓጎል እና የዋጋ መናር አርሶ አደሩ ምርቱን በአግባቡ እንዳያመርት ማነቆ ሆኗል።

​የምግብ ዋስትና መሸርሸር፦ የግብርና ምርታማነት መውረድ በቀጥታ በዜጎች የምግብ ዋስትና ላይ ከፍተኛ አደጋ እየደቀነ ይገኛል።

​የገንዘብ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ወቅት የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት በዓለም አቀፉ የንግድ መስመር ላይ ያስከተለውን ቀውስ በዝርዝር አብራርተዋል። የወሽመጡ መዘጋት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እንዲንር ማድረጉን የጠቀሱት አቶ አህመድ ሽዴ፣ ይህም ሰንሰለታማ የኢኮኖሚ ጫናዎችን መፍጠሩን አስረድተዋል።

​የነዳጅ ዋጋ መናር ያስከተላቸው ዋና ዋና ቀውሶች፦ ​የትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር; ለመስኖ ልማት እና ለግብርና ማቀነባበሪያ; ኢንዱስትሪዎች የሚወጣው ወጪ መናር እና የምግብ ምርቶች ሥርጭት ሂደት መጓተት እና የዋጋ ግሽበት መፈጠሩ የሚሉት ይጠቀሳል።

​አቶ አህመድ ሽዴ አሁን ያለውን ጊዜያዊ ቀውስ ከመቋቋም ባለፈ ዘላቂ መፍትሔዎችን ማምጣት እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል። በተለይም በቀጠናዊ የአቅርቦት ሰንሰለቶች፣ በትላልቅ መጋዘኖች ግንባታ እና በሎጂስቲክስ መሠረተ ልማቶች ላይ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ሊፈስባቸው እንደሚገባና ይህም የአገራትን የመቋቋም አቅም እንደሚያሳድግ ጠቅሰዋል።

​በመጨረሻም ሚኒስትሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው ሰብዓዊ እርዳታ አሰጣጥ ላይ መዋቅራዊ ለውጥ ያስፈልጋል ብለዋል። ሰብዓዊ እርዳታ ዘላቂነት ከሌለውና ጥገኝነትን ከመፍጠር አዙሪት ወጥቶ፣ ከአገራዊ ሥርዓቶች እና አገራት ቅድሚያ ከሚሰጧቸው የልማት አጀንዳዎች ጋር መጣጣም እንዳለበት በጥብቅ አሳስበዋል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ