አምዶች

Logo ከይር ታይምስ

የዲጂታል ዜና እምብርት

የቅርብ ዜና
ምርጫ ቦርድ የዕጩ ይስሃቅ ወልዳይን ራስን ከምርጫ የማግለል ውሳኔ ውድቅ አደረገ “የኮከቡ ሰው” የተሰኘው አዲስ ተውኔት ነገ በዓለም ሲኒማ ለተመልካች ሊቀርብ ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆኑ እስራቶችና የመብት ጥሰቶች አሁንም አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ ገለጸ ፌደራል ፖሊስ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠየቀ የለንደን ሰማይ በደስታ ቀልቷል፡ የአርሰናል የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቅ ያበቃበት ያ ታሪካዊ ምሽት “የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል”፤ መምህር ታዬ ቦጋለ የፖሊሲ ነፃነት ሚስጥር፤ ኢትዮጵያ ቁልፍ መረጃዎቿን በራሷ እጅ ማድረጓ ምን ትርጉም አለው? 'ምንም የሚተርፍ ነገር አይኖርም’ የትራምፕ ለኢራን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ህወሓትን ከሥልጣን ለማስወገድ ያለመው አዲሱ ምክር ቤት እና የጀነራሎቹ ወታደራዊ ስልት ምርጫ ቦርድ የዕጩ ይስሃቅ ወልዳይን ራስን ከምርጫ የማግለል ውሳኔ ውድቅ አደረገ “የኮከቡ ሰው” የተሰኘው አዲስ ተውኔት ነገ በዓለም ሲኒማ ለተመልካች ሊቀርብ ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆኑ እስራቶችና የመብት ጥሰቶች አሁንም አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ ገለጸ ፌደራል ፖሊስ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠየቀ የለንደን ሰማይ በደስታ ቀልቷል፡ የአርሰናል የ22 ዓመታት የዋንጫ ድርቅ ያበቃበት ያ ታሪካዊ ምሽት “የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል”፤ መምህር ታዬ ቦጋለ የፖሊሲ ነፃነት ሚስጥር፤ ኢትዮጵያ ቁልፍ መረጃዎቿን በራሷ እጅ ማድረጓ ምን ትርጉም አለው? 'ምንም የሚተርፍ ነገር አይኖርም’ የትራምፕ ለኢራን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ህወሓትን ከሥልጣን ለማስወገድ ያለመው አዲሱ ምክር ቤት እና የጀነራሎቹ ወታደራዊ ስልት
ዜና / የሀገር ውስጥ ዜና

ፌደራል ፖሊስ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠየቀ

ያፌት ግርማ | May 20, 2026

የፌደራል ፖሊስ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል የመናድ እንቅስቃሴ በማድረግ በጠረጠራቸው 12 ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ መጠየቁ ታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ የወታደራዊ መኮንኖችን እና የሃይማኖት አባቶችን ያካተቱ ሲሆን፣ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ፣ አብርሃም መሀመድ፣ ቀሲስ ክንዳለም አሻግሬ እና ቄስ ኤፍሬም ተክለ ሃናን ጨምሮ 12 ግለሰቦች ይገኙበታል።

ዋዜማ ከፖሊስ የምርመራ ሰነድ ላይ ተመልክቻለሁ እንዳለችው፣ መዝገቡን እየተመለከተው የሚገኘው ችሎት በጉዳዩ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ግንቦት 13 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

​የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን ካሁን ቀደም በፍርድ ቤት ተሰጥቶት በነበረው የምርመራ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን የተለያዩ የምርመራ ሥራዎች እና የሰበሰባቸውን ማስረጃዎች ለችሎቱ በዝርዝር አቅርቧል። ይሁን እንጂ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ የጀመረውን ጥልቅ ማጣራት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ገና እንደሚቀረው አስታውቋል።

​በወንጀል ድርጊቱ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩና እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ሌሎች ግብረ አበሮችን አድኖ ለመያዝ።

​ከተጠርጣሪዎቹ የተያዙ የሰነድና የዲጂታል ማስረጃዎችን በጥልቀት ለመመርመር።

​ችሎቱም የፖሊስን የምርመራ ሂደት እና የተጠርጣሪዎችን መብት መነሻ በማድረግ፣ በቀረበው የተጨማሪ ቀጠሮ ጥያቄ ላይ መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለነገ ግንቦት 13 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

​በፖሊስ የምርመራ ሰነድ ላይ በሰፊው እንደተመላከተው፣ ተጠርጣሪዎቹ አገራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ በርካታ ድብቅ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደነበር ተጠቅሷል። ከእነዚህም መካከል “የኢትዮጵያ ታሪክና ጥቁር አብዮት፤ የአማራ ብሔራዊ ተጋድሎ” የሚል መጠሪያ ያለው ማኒፌስቶ ማዘጋጀታቸው በዋናነት ተጠቅሷል።

ይህ ሰነድ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ የታለመ ስትራቴጂያዊ መመሪያ ሆኖ እንደሚያገለግል ፖሊስ በሰነዱ አመልክቷል።

​ከተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊት አውድ ጋር በተያያዘ የፖሊስ የክስ ሰነድ እጅግ አሳሳቢ የሆኑ የውጭ እና የውስጥ ግንኙነቶችን ይፋ አድርጓል። ተጠርጣሪዎቹ አገሪቱን ለማወክ ካላቸው ዓላማ በመነሳት ከተለያዩ አካላት ጋር የጥቅምና የዓላማ ትስስር ፈጥረዋል ተብሏል።

​ከትጥቅ ቡድኖች ጋር፡ ከፋኖ ታጣቂ ቡድን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መፍጠር።

​ከውጭ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር፡ ከኤርትራ፣ ከግብጽ እና ከሱዳን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት ድጋፍና ስምምነቶችን ለመፍጠር መንቀሳቀስ።

​የሽምቅ ውጊያ ስልጠና፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የከተማ ትጥቅ ትግል እና የከተማ ሽምቅ ውጊያ ለማካሄድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች።

​የመረጃ ደህንነት፡ የመረጃ ማሰባሰብ እና መረጃን የመከላከል ሥልጠናዎችን በሚስጥር ማደራጀት።

​እነዚህን አደገኛ ሥልጠናዎች እና መመሪያዎች በዋትሳፕ (WhatsApp) ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ አማካኝነት በሚስጥር ሲያስተላልፉ እና ሲሰጡ እንደነበር ፖሊስ በምርመራ ሰነዱ ላይ በዝርዝር አስፍሯል።

​ይህ በጀነራሎች እና በሃይማኖት አባቶች ላይ የተመሰረተው የጥርጣሬ መዝገብ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ትኩረትን የሳበ ጉዳይ ሆኗል። ፍርድ ቤቱ ለነገ ግንቦት 13 ቀን በሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ ላይ የፖሊስን የተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጥያቄ ውድቅ ወይም ፍቅድ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ