ታዋቂው የባህላዊ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ |
አምዶች

የዲጂታል ዜናዎች ዕምብርት

የቅርብ ዜና
በአማራ ክልል በደረሰ አስከፊ የመኪና አደጋ የ31 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ33 ላይ ጉዳት ደረሰ ታዋቂው የባህላዊ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በአዲስ አበባ የተጀመረው አስገራሚ የቤት ግንባታ አብዮት! | አዲሱ የዳያስፖራ የቤት ቁጠባ መረጃ (10/70) የብልፅግና ፓርቲ በቁልፍ ክልሎች አሸነፈ፤ ከፊል የምርጫ ውጤቶች ይፋ ሆነዋል የቀይ ባህሩ ቼዝ፣ "የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው" በትሪሊዮኖች የተሰናዳው የ2019 ረቂቅ በጀት ማንን ይታደጋል? የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ረቂቅ በጀት አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላለፈ ክሪስቲያን ኤሪክሰን በድጋሚ በሜዳ ላይ እራሱን ስቶ ወደቀ፤ ጨዋታው ተቋርጧል የቀይ ባህር አዲስ ሰንሰለት፦ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ድንገተኛ የካይሮ ጉብኝት እና የአፍሪካ ቀንድ እጣ ፈንታ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የግብፅ ጉብኝት እና የቀጠናው የፖለቲካ ትኩሳት በአማራ ክልል በደረሰ አስከፊ የመኪና አደጋ የ31 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ33 ላይ ጉዳት ደረሰ ታዋቂው የባህላዊ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በአዲስ አበባ የተጀመረው አስገራሚ የቤት ግንባታ አብዮት! | አዲሱ የዳያስፖራ የቤት ቁጠባ መረጃ (10/70) የብልፅግና ፓርቲ በቁልፍ ክልሎች አሸነፈ፤ ከፊል የምርጫ ውጤቶች ይፋ ሆነዋል የቀይ ባህሩ ቼዝ፣ "የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው" በትሪሊዮኖች የተሰናዳው የ2019 ረቂቅ በጀት ማንን ይታደጋል? የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ2.3 ትሪሊዮን ብር በላይ ረቂቅ በጀት አጽድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስተላለፈ ክሪስቲያን ኤሪክሰን በድጋሚ በሜዳ ላይ እራሱን ስቶ ወደቀ፤ ጨዋታው ተቋርጧል የቀይ ባህር አዲስ ሰንሰለት፦ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ድንገተኛ የካይሮ ጉብኝት እና የአፍሪካ ቀንድ እጣ ፈንታ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የግብፅ ጉብኝት እና የቀጠናው የፖለቲካ ትኩሳት
ዜና / የሀገር ውስጥ ዜና

ታዋቂው የባህላዊ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በያፌት ግርማ | June 16, 2026

የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ በተለይም የጎጃምን ለስላሳና ማራኪ ዜማዎች በማንጎራጎርና ለትውልድ በማሻገር የሚታወቀው አንጋፋውና ተወዳጁ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፉ ተገለጸ።

አርቲስቱ ባደረበት ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በትላንትናው ዕለት በሰላም ማለፉን የቅርብ ቤተሰቦቹና የሙያ አጋሮቹ በታላቅ ሀዘን ገልጸዋል።

​አርቲስት ሰማኸኝ በለው በሀገራችን የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይ በባህላዊው ዘውግ ላይ የማይረሳ አሻራ ጥሎ ያለፈ ከያኒ ነው። የብዙዎቻችንን የልጅነት ጊዜ በትዝታ ወደኋላ የሚወስዱት፣ በገጠርም ሆነ በከተማ በሰፊው የሚደመጡትና ማህበረሰባዊ እሴትን የጠበቁ ስራዎቹ ዘመን የማይሽራቸው ነበሩ።

​"አፈር ለሚበላው ለሚበሰብሰው

ለዚህ ፈራሽ ገላ ቁምጣ መቼ አነሰው"

​እያለ ህይወትንና አለምን የሚመዝንባቸው ጥልቅ ፍልስፍና ያዘሉ ግጥሞቹና ዜማዎቹ ዛሬም ድረስ በሰዎች ልብ ውስጥ ህያው ሆነው ይኖራሉ። በከብት ጥበቃ፣ በደማቅ ሰርግና በተለያዩ ህዝባዊ በዓላት ላይ የሰማኸኝን ሙዚቃ ያልሰማ፣ አብሮ ያልጨፈረና ያላንጎራጎረ የለም ማለት ይቻላል። የባህላዊ የአማርኛ ሙዚቃ ሲነሳ ቀድመው ከአእምሯችን ከሚመጡት ጥቂት ከዋክብት መካከል አንዱ እርሱ ነበር።

​አርቲስት ሰማኸኝ በለው ከሙዚቃ ስራዎቹ ባሻገር በትህትናው፣ በሀገር ፍቅሩና ለባህል ባለው ታማኝነት በሚያውቁት ዘንድ ሁሉ እጅግ ይወደድና ይከበር የነበረ ድንቅ ሰው ነበር። ሞት የማይቀረው የሰው ልጅ ሁሉ እጣ ፈንታ በመሆኑ፣ የሚሆነው ካለመሆን አያመልጥምና እነሆ ስራዎቹንና ውብ ትዝታዎቹን ለህዝቡ አውርሶ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል።

​የአርቲስቱን ስርዓተ ቀብር አስመልክቶ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን፣ የቀብሩ ስነ-ስርዓት የሚፈጸምበትን ጊዜና ቦታ በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል።

​ከይር ታይምስ ለአርቲስት ሰማኸኝ በለው ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም ለሙያ አጋሮቹና ለሙዚቃ አፍቃሪያን በሙሉ መፅናናትንና ጥልቅ ሀዘንን ይመኛል።

​ነፍስህ በሰላም ትረፍ ሰሜ ባላገሩ!

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ