አምዶች

Logo ከይር ታይምስ

የዲጂታል ዜና እምብርት

የቅርብ ዜና
ግንቦት 24 የመንግሥትና የግል ተቋማት ዝግ ሆነው እንደሚውሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች ፈቃድ ለሁሉም ባንኮች ተፈቀደ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ከውድድር መሰረዝ አንድምታዎች የኢትዮጵያ የ51.8 ቢሊዮን ዶላር እዳ — የችግሩ መጠን ወይስ የአያያዝ ጉድለት? የኢቦላ ወረርሽኝ የአፍሪካን ደህንነት እንዴት እየፈተነ ነው? አርቲፊሻል ለውጥ ወይስ እውነተኛ የአካዳሚክ ነፃነት? የጽምዶ እና የመከላከያ ውጥረት እስከም ድረስ ይሆን? ጎጎት ፓርቲ የገዢው ፓርቲ "ስልታዊ" የምርጫ ሕግ ጥሠቶች" ካልታረሙ ራሱን ከምርጫው እንደሚያገል አስጠነቀቀ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምታስገባውን የኤሌክትሪክ ኃይል በእጥፍ ልታሳድግ መኾኑ ተገለጠ 📢 አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ከገንዘብ ሚኒስቴር! ⚠️ ግንቦት 24 የመንግሥትና የግል ተቋማት ዝግ ሆነው እንደሚውሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ወደ ቻይና የሚላኩ ምርቶች ፈቃድ ለሁሉም ባንኮች ተፈቀደ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ከውድድር መሰረዝ አንድምታዎች የኢትዮጵያ የ51.8 ቢሊዮን ዶላር እዳ — የችግሩ መጠን ወይስ የአያያዝ ጉድለት? የኢቦላ ወረርሽኝ የአፍሪካን ደህንነት እንዴት እየፈተነ ነው? አርቲፊሻል ለውጥ ወይስ እውነተኛ የአካዳሚክ ነፃነት? የጽምዶ እና የመከላከያ ውጥረት እስከም ድረስ ይሆን? ጎጎት ፓርቲ የገዢው ፓርቲ "ስልታዊ" የምርጫ ሕግ ጥሠቶች" ካልታረሙ ራሱን ከምርጫው እንደሚያገል አስጠነቀቀ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምታስገባውን የኤሌክትሪክ ኃይል በእጥፍ ልታሳድግ መኾኑ ተገለጠ 📢 አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ከገንዘብ ሚኒስቴር! ⚠️
ፖለቲካ / ምርጫ

ግንቦት 24 የመንግሥትና የግል ተቋማት ዝግ ሆነው እንደሚውሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

ያፌት ግርማ | May 28, 2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ሰላማዊና የተሳካ ለማድረግ፣ በዕለቱ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ዝግ ሆነው እንዲውሉ መወሰኑን አስታወቀ።

ቦርዱ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በሰጠው ይፋዊ መግለጫ እንዳመለከተው፣ ውሳኔው የተላለፈው በምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 161 በተደነገገው «የመተባበር ግዴታ» መሠረት ነው።

የቦርዱ መግለጫ ያካተታቸው ዋና ዋና ዝርዝሮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች በሙሉ ያለምንም የሥራ ጫና ድምፃቸውን መስጠት እንዲችሉ ለማስቻል፡-

 * ማንኛውም የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት በዕለቱ የሥራ ዝግ ያደርጋሉ።

 * በተመሳሳይ መልኩ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ (NGOs) እና የግል ድርጅቶች/ተቋማት በሙሉ ዝግ ሆነው እንዲውሉ ተብሏል።

የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሲባል የሚከተሉት ተቋማት እንቅስቃሴያቸውን እንደማያቋርጡ ተገልጿል፦

 * የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ሆስፒታሎች፣

 * የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ የሆኑት ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና የትራንስፖርት ዘርፎች በተለመደው የዝግ ቀናት አሠራራቸው መሠረት አገልግሎት መስጠታቸውን ይቀጥላሉ።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን ለማስቻል የትራንስፖርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፣ ዜጎች ከድምፅ መስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚጠይቁ ማናቸውንም ሁነቶች (ፕሮግራሞች) እና ዕቅዶች እንዳይይዙ ቦርዱ በጥብቅ አሳስቧል።

የምርጫ ቦርድ በዕለቱ መላው የመራጭነት ካርድ ያላቸው ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ወጥተው መብታቸውን እንዲጠቀሙ ጥሪውን አስተላልፏል።

 

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ