አምዶች

Logo ከይር ታይምስ

የዲጂታል ዜና እምብርት

የቅርብ ዜና
አርቲፊሻል ለውጥ ወይስ እውነተኛ የአካዳሚክ ነፃነት? የጽምዶ እና የመከላከያ ውጥረት እስከም ድረስ ይሆን? ጎጎት ፓርቲ የገዢው ፓርቲ "ስልታዊ" የምርጫ ሕግ ጥሠቶች" ካልታረሙ ራሱን ከምርጫው እንደሚያገል አስጠነቀቀ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምታስገባውን የኤሌክትሪክ ኃይል በእጥፍ ልታሳድግ መኾኑ ተገለጠ 📢 አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ከገንዘብ ሚኒስቴር! ⚠️ ምርጫ ቦርድ የዕጩ ይስሃቅ ወልዳይን ራስን ከምርጫ የማግለል ውሳኔ ውድቅ አደረገ “የኮከቡ ሰው” የተሰኘው አዲስ ተውኔት ነገ በዓለም ሲኒማ ለተመልካች ሊቀርብ ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆኑ እስራቶችና የመብት ጥሰቶች አሁንም አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ ገለጸ ፌደራል ፖሊስ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠየቀ አርቲፊሻል ለውጥ ወይስ እውነተኛ የአካዳሚክ ነፃነት? የጽምዶ እና የመከላከያ ውጥረት እስከም ድረስ ይሆን? ጎጎት ፓርቲ የገዢው ፓርቲ "ስልታዊ" የምርጫ ሕግ ጥሠቶች" ካልታረሙ ራሱን ከምርጫው እንደሚያገል አስጠነቀቀ ኬንያ ከኢትዮጵያ የምታስገባውን የኤሌክትሪክ ኃይል በእጥፍ ልታሳድግ መኾኑ ተገለጠ 📢 አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ከገንዘብ ሚኒስቴር! ⚠️ ምርጫ ቦርድ የዕጩ ይስሃቅ ወልዳይን ራስን ከምርጫ የማግለል ውሳኔ ውድቅ አደረገ “የኮከቡ ሰው” የተሰኘው አዲስ ተውኔት ነገ በዓለም ሲኒማ ለተመልካች ሊቀርብ ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለታዳጊ አገራት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠየቁ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚፈጸሙ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆኑ እስራቶችና የመብት ጥሰቶች አሁንም አሳሳቢ መሆናቸውን ኢሰመኮ ገለጸ ፌደራል ፖሊስ በእነ ጀነራል አስናቀው ሲሳይ ላይ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠየቀ
ነፃ ሃሳብ / የምሁራን መድረክ

አርቲፊሻል ለውጥ ወይስ እውነተኛ የአካዳሚክ ነፃነት?

May 24, 2026

ሰሞኑን በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ የተደረገው አቅጣጫ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አመራሮች አመዳደብ ቀድሞ ከነበረው የብሔር ስብጥር አሰራር በመውጣት በችሎታ በቻ ተወዳድረረው የሚመደቡበት አሠራር ሊዘረጋ እንደሆነ ያሳያል።

ይህ ውሳኔ በአንደኛ እይታ እንደ ትልቅ “ሪፎርም” እና ተስፋ ሰጪ እርምጃ ሊታይ ይችላል። ይሁን እንጂ፣ የሀገሪቱን ነባራዊ የፖለቲካ ልምድ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የተወሳሰበ ውድቀት መነሻ በማድረግ፣ ጉዳዩን ይበልጥ በጥልቀት ስንመረምረው፣ ከጀርባው ያሉትን ስር የሰደዱ ጥያቄዎች እና ስጋቶች መገንዘብ ያስፈልጋል።

የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላለፉት በርካታ አስርት ዓመታት የብሔር ፖለቲካ መፈልፈያ፣ የፓርቲ ካድሬዎች መደበቂያ እና የብቃት ማነስ ማሳያ ሆነው መቆየታቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። አሁን ላይ “ከብሔር ስብጥር አሰራር ወጥተን በችሎታ ልንመድብ ነው” ተብሎ የሚነገረው ትረካ፣ ተቋማቱ አስከፊ የጥራት መውረድ አጋጥሟቸው፣ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ተማሪዎች ሳይሆኑ ተቋማቱ ራሳቸው የወደቁ መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ የመጣ የኋሊት ጩኸት ነው። ይህ መዘግየት በራሱ የፖለቲካው ውሳኔ የትምህርትን መዋቅር ምን ያህል እንዳደቀቀው ማሳያ ነው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎችን “ከማንኛውም የፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ማድረግ” ስለሚለው አጀንዳ ደጋግመው ይናገራሉ። ይሁን እንጂ፣ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ “ክፍት ውድድር” የሚባሉ የቅጥር ማስታወቂያዎች ራሳቸው በፖለቲካ ታማኝነት (Political Loyalty) እና በውስጥ መስመር ውሳኔዎች የሚጠለፉባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው። ተቋማቱ በተግባር ነፃነታቸው ሳይረጋገጥ፣ በወረቀት ላይ በሚደረግ “ፈተና እና ውድድር” ብቻ አመራር ለመቀየር መሞከር፣ የድሮዎቹን ካድሬዎች በአዲሱ ገዥ መደብ ፍላጎት በሚስማሙ አዳዲስ “ቴክኖክራቶች” ከመተካት የዘለለ መዋቅራዊ ለውጥ ላያመጣ ይችላል። እውነተኛ ነፃነት የሚለካው አመራሩ በሚመረጥበት መንገድ ብቻ ሳይሆን፣ ተቋማቱ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው በራሳቸው መተዳደር (Autonomy) ሲችሉ ብቻ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎች በአሁኑ ወቅት የተጋረጡባቸው ችግሮች የአመራሮቹ የብሔር ስብጥር ብቻ አይደለም። ተቋማቱ በከፍተኛ የበጀት እጥረት፣ በደህንነት ስጋቶች፣ በካምፓስ ውስጥ አለመረጋጋት፣ እና በተመራማሪዎች የኑሮ መጓደል ሳቢያ ምሁራንን እያጡ ያሉ አቅመ-ቢስ መዋቅሮች ሆነዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ (ለምሳሌ በዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ ቀውሶች ሳቢያ በሚከሰት የኢኮኖሚ ጫና) የሚታየው የዋጋ ንረት እና የሪሶርስ እጥረት ባለበት ሁኔታ፣ የአመራር መምረጫ መስፈርቱን “በእውቀትና ችሎታ” ላይ ብቻ አደረግን ማለት ብቻውን ተቋማቱን የጥናትና ምርምር ማዕከል ሊያደርጋቸው አይችልም። መዋቅራዊ እና ፋይናንሺያል ድጋፍ ሳይኖር፣ ብቁ መሪዎችን ብቻ ወደ ወንበር ማምጣት በባዶ ሞተር ላይ ጎበዝ ሾፌር የማስቀመጥ ያህል ነው።

 

Recommended
Bottom Advertisement
Learn More

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የከይር ታይምስ ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ